2021-01-15 12:17:16 | by Philosophi
ኮምፒውተሮች ሁልጊዜ ለተለያዩ አይነት ውስጣዊና ውጫዊ ጥቃቶች የመጋለጥ እድላቸው ሰፊ ነው፡፡ በመሆኑም ሁልጊዜ የሚጠቀምባቸውን ኮምፒውተሮች አጠቃላይ ባህሪ መረዳት፣ በየጊዜው ማሻሻያ ሊደረግባቸው የሚገባና መቀየር ያለባቸውን ስርዓቶች ማወቅ እንዲሁም መረጃዎች እንዳይጠፉ ጥንቃቄ መውሰድ ይገባል፡፡ ከዚህ አንጻርም ጠቃሚ ፋይሎችን መጠባበቂያ መያዝ የኮምፒውተር ፕሮግራሞች ሥርዓት ለደህንነት ሥጋት እንዳይጋለጥ ማሻሻያና ለውጥ ማድረግ አንቲ-ቫይረስ ሶፍትዌሮችን መጠቀም፣ በየጊዜው መተግበሪያዎችን ማሻሻል እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ አጠቃላይ የኮምፒውተር ስርዓትን ስካን ማድረግ አጥፊ ሶፍትዌሮችን የሚከላከሉ ፀረ-አጥፊ ሶፍትዌሮችን መጠቀም እና ቢያንስ በወር አንድ ጊዜ ስካን ማድረግ እንዲሁም የተመጠነ የፋይል አስተዳደር መተግበር እና ዲስኮችን በየጊዜው ማፅዳት እንደሚገባ ከኢንፎርሜሽን እና መረብ ደህንነት ኤጀንሲ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል፡፡
Last updated 2021-01-15 12:19:06
Last updated 2021-01-15 12:17:16
Last updated 2021-01-15 12:14:42