2021-01-15 12:14:42 | by Philosophi
ማይክሮሶፍት ያቀረበው ሥርዓት ለሊኑክስ ተጠቃሚዎች የሚሆን ኢንድ ፖይንት ዲቴክሽን ሪስፖንስ የተባለ የደህንነት ማስጠበቂያ ነው ተብሏል፡፡ የበይነ መረብ ጥቃት መከላከያ ሥርዓቱ ስጋቶችን ለመቀነስ፣ ተከታታይ በሆነ መልኩ የኮምፒውተር ሲስተሞችን ለመቆጣጣር እና አፋጣኝ ምላሽ ለመስጠት ከፍተኛ ድርሻ እንዳለው ተገልጿል፡፡ በማይክሮሶፍት የቀረበው አዲሱ የኢንድፖይንት ዲቴክሽን ሪስፖንስ ስርዓት የመረጃ መንታፊዎች የሊኑክስ ሰርቨሮችን ኢላማ በማድረግ ሊፈጽሙ ያሰቡትን የጥቃት እንቅስቃሴ መለየት የሚያስችል ሲሆን በዚህም ለአድሚኖች እና ለበይነ መረብ ደህንነት ቡድን ድጋፍ እንደሚሰጥ ታውቋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ስርዓቱ አውቶማቲክ በሆነ መልኩ ለደህንነት መጠበቂያ አካላት የማንቂያ ድምጽ በማሰማት ጉዳቶችን ለመቀነስ እና ለመከላከል የሚያግዝ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ ይህን ለመጠቀመም የሲስተም አድሚኖች በሊኑክስ የኢንተርፕራይዝ መገልገያቸው ላይ አንስብል ወይም ፑፔት እንዲሁም በማንኛውም ሌላ የሊኑክስ ውቅር አድሚኒስትሬቲቭ መሣሪያ እገዛ ሊተገብሩት እና ሊያዋቅሩት እንደሚችሉ ታውቋል፡፡ በመሆኑም ተጠቃሚዎች ከዚህ ቀደም የማይክሮሶፍት ዲፌንደር ኢንድፖይንትን ለሊኑክስ እየተጠቀሙ ከሆነ አዲሱን ስሪት (version 101.18.53) ወይም ከዚያ በላይ የሆኑትን ያለምንም እንከን ማዘመን እንደሚችሉ ማይክሮሶፍት የምርት ሥራ አስኪያጅ ቶመር ሄቭሊን መግለጻቸውን ኢመደኤ ዘግቧል። #FBC
Last updated 2021-01-15 12:19:06
Last updated 2021-01-15 12:17:16
Last updated 2021-01-15 12:14:42