አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 21፣ 2010 ኤፍቢሲ ተመራማሪዎች የፀረ ሰብል ተባዮችን ዓይነት የሚለይ የስማርት ስልክ መተግበሪያ ወይንም አፕሊኬሽን መስራታቸውን አስታወቁ፡፡
አፕሊኬሽኑ የሚሰራው ሰብሎቹን ፎቶ በማንሳት ሲሆን ይህንንም ተከትሎ የተባዩን ዓይነት መለየት ይችላል ተብሏል፡፡
አፕሊኬሽኑ በቻይና የሚገኘው አካዳሚ ሳይንስ አማካኝነት የሙከራ ሂደት አድርጓል፡፡ በዚህም እስከአሁን ድረስ 50 የሚደርሱ የሩዝ ተባዮችን መለየት መቻሉን ተቋሙ አረጋግጧልdf፡፡
የፕሮግራሙ ተመራማሪ የሆኑት ቻይናዊ በሀገሪቱ የሚገኙ አምራቾች የፀረ ሰብል ተባዮችን በመለየት ትክክለኛውን ፀረ ተባይ እንዲጠቀሙ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡
አፕሊኬሽኑ ሰው ሰራሽ የማሰብ አቅም ያለው ቴክኖሎጂ ያካተተ ሲሆን ከአንድ ሺህ በላይ ፎቶዎችን በመረጃ መያዣው ውስጥ ተካተዋል፡፡ በዚህ መነሻነትም የተነሳውን ፎቶ ማህደሩ ውስጥ ከተካተቱ ጋር በማመሳከር ዓይነቱን ያሳውቃል ተብሏል፡፡
ተመራማሪዎቹ አዲሱን መተግበሪያ በቅርቡ በበቆሎ፣ በስንዴና በሌሎች የሰብል ምርቶች ላይ እንደሚሞክሩት ገልጸዋል፡፡
You would most likely not travel to another country witho ....
View details »
ETHIOPIA Addis Ababa
haile gebre selassie street, 22 mazoria behind getahun beshah blg.
Mon - Fri: 8:30AM – 5:30PM
Saturday: 8:30 AM – 1:30 PM
Sunday: 9:00 AM – 2;00 PM